ወላይታ ድቻ ግብ ጠባቂ አስፈርሟል

ለሁለተኛው ዙር ካለበት መጥፎ የውጤት ጉዞ ለመላቀቅ በማለም አዳዲስ ተጫዋቾችን ወደ ክለቡ እየቀላቀለ የሚገኘው ወላይታ ድቻ አሁን ደግሞ አራተኛ ፈራሚውን ወደ ክለቡ በመቀላቀል ደረጄ ዓለሙን አስፈርሟል።

የቀድሞው የሰበታ ከተማ፣ ዳሽን ቢራ እና አዲስ አበባ ከተማ ግብ ጠባቂ ደረጄ ዓለሙ ከዚህ ቀደም በኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ውስጥ ተካቶ መጫወት የቻለ ሲሆን በዘንድሮው የውድድር አመት ደግም በከፍተኛ ሊጉ ክለቡ አማራ ውሀ ስራ (አውስኮድ) ቆይታን ካደረገ በኋላ የፕሪምየር ሊጉን ክለብ ወላይታ ድቻ በይፋ መቀላቀል ችሏል። ተጫዋቹ ቋሚ ተሰላፊ ለመሆን ከታሪክ ጌትነት እና መኳንንት አሸናፊ ብርቱ ፈተናም የሚጠብቀው ይሆናል፡፡

በቅርቡ ደጉ ደበበ፣ አንተነህ ጉግሳ እና አላዛር ፋሲካን ያስፈረመው ክለቡ ከነኚህ ውጪ ተጨማሪ ተጫዋቾችን እንደማያስፈርም ተሰምቷል።


© ሶከር ኢትዮጵያ

በድረ-ገጻችን ላይ የሚወጡ ጽሁፎች ምንጭ ካልተጠቀሱ በቀር የሶከር ኢትዮጵያ ናቸው፡፡ እባክዎ መረጃዎቻችንን በሚጠቀሙበት ወቅት ምንጭ መጥቀስዎን አይዘንጉ፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *