ፋሲል ከነማ የወዳጅነት ጨዋታ አዘጋጀ

ዐፄዎቹ የተፈናቀሉ ወገኖችን ለመርዳት ነገ በያያ ቪሌጅ ከሱዳኑ አል ሜሪክ ጋር የገቢ ማሰባሰቢያ ጨዋታ ሊያደርጉ ነው።

የፋሲል ከነማ ስፖርት ክለብ ይፋዊ የፌስ ቡክ ገፅ ይዞት በወጣው መረጃ መሰረት በመላው ኢትዮጵያ ከቅያቸው ለተፈናቀሉ እና ችግር ለደረሰባቸው ወገኖች ገቢ ለማሰባሰብ ይረዳ ዘንድ ክለቡ ከሱዳኑ አል ሜሪክ ጋር ነገ ረቡዕ መጋቢት 11 ቀን በ9:00 በያያ ቪሌጅ የገቢ ማሰባሰቢያ ጨዋታ ያደርጋል።

የቀድሞው የፌስቡክ ገፃችን በኛ ቁጥጥር ስር የማይገኝ በመሆኑ አዲሱ ገፃችንን ሊንኩን በመከተል ላይክ ያድርጉ – facebook.com/SoccerEthiopia

ፋሲል ከነማ ጨዋታውን በቅድሚያ በአዲስ አበባ ስታድየም የማከናወን ዕቅድ የነበረው ቢሆንም ለኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን በደብዳቤ ጥያቄ ቢያቀርብም ተቀባይነት አላገኘም። ፌዴሬሽኑ ከ23 ዓመት በታች የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ጨዋታ ሀሙስ የሚካሄድ በመሆኑ ሜዳው ከ48 ሰዓት በፊት ከጨዋታ ነጻ መሆን ስላለበት ነው ይሁንታውን ያልሰጠው።

በመሆኑም ክለቡ በአዲስ አበባ በርካታ ደጋፊዎችን የሚያስተናግድ አማራጭ ስታድየም ባለማግኘቱ የወዳጅነት ጨዋታውን በሱሉልታ ያያ ቪሌጅ ለማከናወን መገደዱን የፌስቡክ ገፁ ጨምሮ ገልጿል።


© ሶከር ኢትዮጵያ

በድረ-ገጻችን ላይ የሚወጡ ጽሁፎች ምንጭ ካልተጠቀሱ በቀር የሶከር ኢትዮጵያ ናቸው፡፡ እባክዎ መረጃዎቻችንን በሚጠቀሙበት ወቅት ምንጭ መጥቀስዎን አይዘንጉ፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *