የቀድሞው የኢትዮጵያ ቡና አሰልጣኝ ወደ ጊኒ አመሩ

ባለፈው ዓመት ከኢትዮጵያ ቡና ፍቃድ ውጪ ከሀገር በመውጣት ጠፍተው በቀሩት ሰርቢያዊው አሰልጣኝ ኮስታዲን ፓፒች ምትክ የኢትዮጵያ ቡና አሰልጣኝነት ወንበር የተረከቡት ፈረንሳዊው አሰልጣኝ ዲዲዬ ጎሜስ ከኢትዮጵያ ቡና ከተሰናበቱ በኋላ ለጥቂት ጊዜ ያለ ስራ ቆይተው የጊኒው ሆሮያን ለማሰልጠን ተስማምተዋል።

ከዚ በፊት ራዮን ስፖርትስ፣ ኮተን ስፖርትስ እና ጄሴኤም ስኪዳ ያሰለጠኑት ዲዲዬ ጎሜስ ባለፈው ዓመት ኢትዮጵያ ቡናን አሻሽለው ለዚህ የውድድር ዓመት ተስፋ ተጥሎባቸው የነበረ ቢሆንም ከጥሩ አጀማመር ቀስ በቀስ ወደ ውጤት ቀውስ ማምራታቸውን ተከትሎ የኋላ ኋላ መሰናበታቸው ይታወሳል።

የቀድሞው የፌስቡክ ገፃችን በኛ ቁጥጥር ስር የማይገኝ በመሆኑ አዲሱ ገፃችንን ሊንኩን በመከተል ላይ ያድርጉ – facebook.com/SoccerEthiopia

ያለፈው ዓመት የጊኒ ቻምፒዮናት ናሽናል አሸናፊው እና የዘንድሮውንም ውድድር በ23 ነጥቦች እየመራ የሚገኘው ሆሮያ በታሪኩ ለሁለተኛ ጊዜ ለቻምፒንስ ሊግ ሩብ ፍፃሜ መብቃት ቢችልም ፈረንሳዊው አሰልጣኝ ፓትሪስ ኖቬውን በትላንትናው ዕለት ማሰናበቱን ተከትሎ ሌላኛውን ፈረንሳዊ በመንበሩ ላይ ሾሟል።


© ሶከር ኢትዮጵያ

በድረ-ገጻችን ላይ የሚወጡ ጽሁፎች ምንጭ ካልተጠቀሱ በቀር የሶከር ኢትዮጵያ ናቸው፡፡ እባክዎ መረጃዎቻችንን በሚጠቀሙበት ወቅት ምንጭ መጥቀስዎን አይዘንጉ፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *