ለኢትዮጵያ ከ20 ዓመት በታች ብሔራዊ ቡድን ዋና አሰልጣኝ ተሹሟል

በኢትዮጵያ ቡና ያለፉትን ሶስት ዓመታት በወጣት ቡድን አሰልጣኝነት ሲሰራ የቆየው አሰልጣኝ ዮሴፍ ተስፋዬ ከ20 ዓመት በታች ብሔራዊ ቡድን አሰልጣኝ በመሆን ተሾመ።

በአስመራ ለሚካሄደው “የሠላም እና ወዳጅነት ከ20 ዓመት በታች ውድድር” ዝግጅት ካለፈው ሳምንት ጀምሮ አሰልጣኝ ለመቅጠር ፌዴሬሽኑ ማስታወቂያ ማውጣቱ የሚታወስ ሲሆን በዚህ መሠረት አሰልጣኝ ዮሴፍ ተስፋዬን ለዋና አሰልጣኝነት መርጧል።

ኢትዮጵያ ቡና፣ ሀዋሳ ከተማ፣ ሙገር ሲሚንቶ እና ቅዱስ ጊዮርጊስ ለመሳሰሉ ክለቦች እንዲሁም ለብሔራዊ ቡድን እስከ 1990ዎቹ መጨረሻ በተጫዋችነት ያሳለፈውና ያለፉትን ሶስት ዓመታት ደግሞ የኢትዮጵያ ቡና ከ17 እና ከ20 ዓመት በታች ቡድንን ሲመራ የቆየው አሰልጣኙ በይፋ የብሔራዊ ቡድኑ አሰልጣኝ መሆኑ የተገለፀ ሲሆን በቅርቡ ተጫዋቾችን በመሰብሰብ ወደ ዝግጅት እንደሚገባ እና ረዳት አሰልጣኞችንም ጭምር እንደሚያሳውቅ ይጠበቃል፡፡

የቀድሞው የፌስቡክ ገፃችን በኛ ቁጥጥር ስር የማይገኝ በመሆኑ አዲሱ ገፃችንን ሊንኩን በመከተል ላይ ያድርጉ – facebook.com/SoccerEthiopia


© ሶከር ኢትዮጵያ

በድረ-ገጻችን ላይ የሚወጡ ጽሁፎች ምንጭ ካልተጠቀሱ በቀር የሶከር ኢትዮጵያ ናቸው፡፡ እባክዎ መረጃዎቻችንን በሚጠቀሙበት ወቅት ምንጭ መጥቀስዎን አይዘንጉ፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *