ለሞገስ ታደሰ የህክምና ወጪ ከተመልካች የገንዘብ ድጋፍ ተደረገ

ለሞገስ ታደሰ የህክምና ወጪ እንዲውል ፌዴሬሽኑ በወሰነው ውሳኔ መሠረት ዛሬ በአዲስ አበባ ስታድየም በኢትዮጵያ እና ዩጋንዳ መካከል በተካሄደው ጨዋታ ከተመልካች ከ90 ሺህ ብር በላይ ገንዘብ ተገኝቷል።

ከባለፈው ዓመት ጀመሮ ባጋጠመው ጉዳት ምክንያት ከሜዳ የራቀው ሞገስ ከህመሙ ለማገገም እንዲችል የስፖርት ቤተሰቡን ድጋፍ መጠየቁን ተከትሎ የተለያዩ ድጋፎች እየተደረጉለት ይገኛል። ዛሬ በአዲስ አበባ ስታዲየም በኢትዮጵያ እና ዩጋንዳ መካከል በተካሄደው ጨዋታም 3235 ተመልካች የገባ ሲሆን ከዚህም 97,515 ሺህ ብር ገቢ እንደተገኘ ታውቋል።

ይህ ድጋፍ ተጠናክሮ በቀጣዩ ሳምንት በሚደረጉ የሊጉ ጨዋታዎች ላይ መሰል ተጨማሪ ገቢ ለማግኘት እንደታሰበ ለማወቅ ችለናል።


© ሶከር ኢትዮጵያ

በድረ-ገጻችን ላይ የሚወጡ ጽሁፎች ምንጭ ካልተጠቀሱ በቀር የሶከር ኢትዮጵያ ናቸው፡፡ እባክዎ መረጃዎቻችንን በሚጠቀሙበት ወቅት ምንጭ መጥቀስዎን አይዘንጉ፡፡