ጌታነህ ከበደ ለህክምና ወደ ህንድ ይጓዛል

በልምምድ ላይ እያለ ጉዳት በጉልበቱ ላይ ጉዳት የገጠመው ጌታነህ ከበደ ለህክምና ወደ ህንድ ይጓዛል

ደደቢትን በመልቀቅ በዘንድሮ ዓመት ቅዱስ ጊዮርጊስን የተቀላቀለው ጌታነህ ከበደ በ17ኛ ሳምንት የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ክለቡ አዳማ ከተማን 1-0 ሲያሸንፍ ብቸኛዋን ጎል ባስቆጠረ ማግስት በልምምድ ስፍራ ባጋጠመው የጉልበት ጉዳት ምክንያት ለህክምና ወደ ህንድ ሊያቀና መሆኑን ክለቡ አሳውቋል።

እንደ ክለቡ ገለፃ ቅዱስ ጊዮርጊስ በተደጋጋሚ ተጫዋቾቹ ሲጎዱ ለህክምና ወደሚልክበት ህንድ አፖሎ ሆስፒታል በማምራት የጉልበት ህክምናን የሚያደርግ ሲሆን በቀጣይ ሳምንት ረቡዕም ወደ ስፍራው ያመራል።

“ክለቤን በተገቢው ወቅት ማገልገል ባለመቻሌ ቁጭት ውስጥ ከቶኛል። ሆኖም የደረሰብኝ ጉዳት በአግባቡ መታከምን የሚጠይቅ ስለሆነ ያን ለማድረግ እሄዳለው። በሚገባ አገግሜ ስመለስ የተሻለ ነገርን በተነሳሽነት እሰራለሁ።” ሲል ለሶከር ኢትዮጵያ ገልጿል፡፡

ጌታነህ ከበደ በውድድር ዓመቱ ለቅዱስ ጊዮርጊስ በሊጉ ሦስት ጎሎችን አስቆጥሯል።


© ሶከር ኢትዮጵያ

በድረ-ገጻችን ላይ የሚወጡ ጽሁፎች ምንጭ ካልተጠቀሱ በቀር የሶከር ኢትዮጵያ ናቸው፡፡ እባክዎ መረጃዎቻችንን በሚጠቀሙበት ወቅት ምንጭ መጥቀስዎን አይዘንጉ፡፡