ፌዴሬሽኑ ክለቦች የቀጥታ ስርጭትን ለማስተላለፍ ፍቃድ መጠየቅ እንዳለባቸው አሳሰበ

የኢትዮጵያ እግርኳስ ፌዴሬሽን ያለ ፍቃድ ውድድሮችን በራዲዮም ሆነ በቴሌቪዥን በቀጥታ ስርጭት የሚያስተላልፉ ክለቦች ላይ ቅጣት እንደሚጥል በጥብቅ አሳውቋል።

ፌዴሬሽኑ የቀጥታ ስርጭት የሚያስተላልፉ ክለቦች ፍቃድ በመውሰድ እንዲያስተላልፉ በደብዳቤ የጠየቀ ሲሆን ይህን ተግባራዊ ሳያደርጉ ሲያስተላልፉ በተገኙ ክለቦች ላይ ጠበቅ ያለ ቅጣት እንደሚያስተላልፍ አሳውቋል።

ከዚህ ቀደም ፌዴሬሽኑ በተመሳሳይ መልኩ የቀጥታ ስርጭት እንዳይተላለፍ እግድ አውጥቶ የነበረ ቢሆንም በኋላ ላይ የቀጥታ ስርጭት ከሚያስተላለፉ ተቋማት ጋር ፌዴሬሽኑ ባዘጋጀው የውል ስምምነት ለመፈፀም በመስማማት በቲቪም ሆነ በሬዲዮም እያስተላለፉ መቆየታቸው ይታወቃል።


© ሶከር ኢትዮጵያ

በድረ-ገጻችን ላይ የሚወጡ ጽሁፎች ምንጭ ካልተጠቀሱ በቀር የሶከር ኢትዮጵያ ናቸው፡፡ እባክዎ መረጃዎቻችንን በሚጠቀሙበት ወቅት ምንጭ መጥቀስዎን አይዘንጉ፡፡