‹‹ በትክክል የሴካፋ ግባችንን አሳክተናል›› አሰልጣኝ ዮሃንስ ሳህሌ

የኢትዮጵያ የሴካፋ ጉዞ በመለያ ምቶች ግማሽ ፍፃሜው ላይ ተገትቷል፡፡ ከጨዋታው በኋላ አስተያየታቸውን የሰጡት አሰልጣኝ ዮሃንስ ሳህሌ የሴካፋ ግባቸውን ማሳካታቸውን ተናግረዋል፡፡

‹‹ የመጀመርያ አላማችን የነበረው ሴካፋን ለተጫዋቾቼ ልምድ ማግኛ እንዲጠቅመን ነበር፡፡ በዚህ በኩል ግባችንን አሳክተናል፡፡ ለብሄራዊ ቡድን በትልቅ ደረጃ የመጫወት ልምድ ለሌላቸው ተጫዋቾች ውድድሩ አስቸጋሪ ነበር፡፡ በተጨማሪም አቅማችን እስከፈቀደው ድረስ መጓዝ ችለናል፡፡ ከ12 ሀገራት መካከል 3 ወይም 4ኛ መውጣት ትልቅ ነገር ነው፡፡ ›› ብለዋል፡፡

 

‹‹በተከላካዮቼ ብቃት ኮርቻለሁ›› ሚቾ

‹‹ ይህ እግርኳስ ነው፡፡ መሸናነፍም የጨዋታ አንዱ አካል ነው፡፡ በማሸነፋችን ደስ ቢለኝም ደስታዬን በጭፈራ መግለጽ አልችልም፡፡ ››

 

ቡድናቸው ለ4 ጨዋታ ግብ አለማስተናገዱ

‹‹ በተከላካዮቼ ብቃት ኮርቻለው፡፡ በኬንያ ከተሸነፍን በኋላ ከዛንዚባር ፣ ቡሩንዲ ፣ ማላዊ እና ዛሬ ደግሞ ከኢትዮጵያ ጋር ለ120 ደቂቃ ግብ አላስተናገድንም፡፡ ››

ስለ ኢትዮጵያ

‹‹ ኢትዮጵያ እንዲህ ትፈትነናለች ብዬ አላሰብኩም፡፡ ተጋጣሚያችን በታክቲኩ አቀራረቡ ጥሩ ነበር፡፡ ጥሩ 11 ተጫዋቾች ይዘው ገብተዋል፡፡ ከዚህም በላይ 12ኛ ተጫዋች የሆነው ደጋፊያቸው ከጎናቸው ነበር፡፡ አዲስ አበባ ላይ መጫወት ከባድ እንደመሆኑ ጨዋታው ለኛ ቀላል አልነበረም፡፡ ››

ስለ ፍፃሜው

‹‹ በ12 ቀናት ውስጥ 5 ጨዋታ በማድረጋችን ከድካም ለማገገም አስቸጋሪ ነው፡፡ የቀረችውን ጊዜ ተጠቅመን በፍፃሜው የተሻለ ቡድን ይዘን በመቅረብ ዋንጫውን ማንሳት ይጠበቅብናል፡፡››

ስለ ዮሃንስ ሳህሌ

‹‹ ለኢትዮጵያ አሰልጣኝ ያለበኝን ክብር መግለፅ እፈልጋለሁ፡፡ ዮሃንስ ጥሩ አሰልጣኝ ነው፡፡ እኔ ለኢትዮጵያውያን የቤተሰብ ያህል ስለሆንኩ በማንኛውም ነገር ከጎናችሁ ነኝ፡፡ ››

 

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *