የኢትዮጵያ ከ17 አመት በታች ሴቶች ብሄራዊ ቡድ በሴፕቴምበር 2016 በጆርዳን አስተናጋጅነት ለሚካሄደው የአለም ከ17 አመት በታች ሴቶች ዋንጫ ላይ ለመካፈል የሚያደርገውን የማጣርያ ጨዋታ በታህሳስ መጨረሻ ከካሜሩን ጋር በመጫወት ይጀምራል፡፡
የታዳጊ ቡድኑ አሰልጣኝ አስራት አባተ በተለያዩ ክልሎች ተዟዙረው 34 ተጫዋቾችን ከክለቦች እና አካዳሚዎች የመረጡ ሲሆን እስከ ነገ ድረስ እንዲሰባሰቡ ጥሪ ቀርቦላቸዋል፡፡
ቡድኑ ረቡእ ጠዋት ልምምድ የሚጀመር ሲሆን አሰልጣኝ አስራት ከዝግጅት በኋላ 10 ተጫዋቾችን ቀንሰው የመጨረሻ 24 ተጫዋቾችን ያሳውቃሉ፡፡
ከተመረጡት 34 ተጫዋች አመዛኞቹ ከክለቦች የተመረጡ በመሆኑ በቡድኑ ዝግጅት ምክንያት የኢትዮጵያ ሴቶች ፕሪሚየር ሊግ ሊቋረጥ ይችላል፡፡ በዚህ ዙርያ ለሶከር ኢትዮጵያ አስተያየታቸውን የሰጡት የፌዴሬሽኑ የህዝብ ግንኙነት አቶ ወንድምኩን አላዩ ውድድሩ እንዳይቋረጥ አማራጮችን እንደሚጠቀሙ ገልፀዋል፡፡ ‹‹ ክለቦች ፍቀደኛ ከሆኑ ቡድኑ እየተዘጋጀ የሊጉ ጨዋታዎች ሲደረጉ ወደየክለቦቻቸው መሄድ ይችላሉ፡፡ ይህ ካልተሳካ ደግሞ በርካታ ተጫዋች ያስመረጡ ክለቦች የሚያደርጓቸው የሊግ ጨዋታዎች ለሌላ ጊዜ ይራዘማሉ፡፡ ሁሉንም ነገር በጊዜ ሒደት የምየው ይሆናል፡፡›› ብለዋል፡፡
ለኢትዮጵ ከ17 አመት በታች ብሄራዊ ቡድን የተመረጡት ተጫዋቾች የሚከተሉት ናቸው፡-
ግብ ጠባቂዎች
ፅዮን ግርማ – ኢትዮጵያ ቡና
የምወድሽ ይርዳቸው – ጥሩነሽ ዲባባ አካዳሚ
ልዩወርቅ መንበረ – አምቦ ጎል ፕሮጀክት
ተከላካዮች
ሳምራዊት ኃይሉ – መከላከያ
ምህረት ኃይሉ – መከላከያ
በላይነሽ ልንገርህ – ኢትዮጵያ ቡና
ካሰች ቲጋ – ኢትዮጵያ ቡና
ቅድስት በቃሉ – ሀዋሳ ከነማ
አዲስ ግዛው – ኤክትሪክ
ስመኝ ምህረቴ – ዲላ ከነማ
ርብቃ ጣሰው – ሲዳማ ቡና
አይናለም ከበደ – ድሬዳዋ ከነማ
ማህደር ባዬ – አዳማ ከነማ
አማካዮች
መንደሪን አንድይሁን – ዲላ ከነማ
እመቤት ለገሰ – መከላከያ
እርሻን ብርሃኑ – መከላከያ
የምስራች ላቀው – መከላከያ
ማእድን ሳህሉ – ኢትዮጵያ ቡና
ሮማን ገብረመድህን – ሀዋሳ ከነማ
ቤተልሄም አሰፋ – ቅድስት ማርያም
ሰላም ተክላይ – ቅድስት ማርያም
በጸሎት ልኡልሰገድ – ጥሩነሽ ዲባባ አካዳሚ
ፀጋ ብሩ – አምቦ ጎል ፕሮጀክት
አረጋሽ ካሳ – ኢትዮጵያ ወጣቶች አካዳሚ
ሲሳይ ገብረዋሃድ – ኢትዮጵያ ወጣቶች አካዳሚ
አጥቂዎች
ሳራ ይርዳው – ኢትዮጵያ ቡና
ምርቃት ፈለቀ – ሀዋሳ ከነማ
እድላዊት ለማ – ቅድስት ማርያም
ትኑር ፍስሃ – ጥሩነሽ ዲባባ አካዳሚ
ጤና ዋኩማ – ጥሩነሽ ዲባባ አካዳሚ
ሳራ ነብሶ – አምቦ ጎል ፕሮጀክት
ትመር ጠንክር – ቅዱስ ጊዮርጊስ
ድንቅነሽ በቀለ – ድሬዳዋ ከነማ
ሜላት ደመቀ – አዳማ ከነማ
© soccerethiopia.net