በኢትዮጵያ ፕሪሚር ሊግ 7ኛ ሳምንት የመጨረሻ ጨዋታ ቅዱስ ጊዮርጊስ ደቢትን አሸንፎ አዳማ ከነማን በቅርብ ርቀት መከታተሉን ቀጥሎበታል፡፡
11፡30 በተደረገው ጨዋታ ቅዱስ ጊዮርጊስ በአዳነ ግርማ የ27ኛ ደቂቃ ግብ የመጀመርያውን አጋማሽ 1-0 እየመራ አጠናቋል፡፡ ዩጋንዳዊው ብሪያን ኡሞኒ በጨዋታው የመጨረሻ ደቂቃ የቅዱስ ጊዮርጊስን መሪነት አስተማማኝ ያደረገች ግብ አስቆጥሮ ጨዋታው በቅዱስ ጊዮርጊስ 2-0 አሸናፊነት ተጠናቋል፡፡
ድሉን ተከትሎ ቅዱስ ጊዮርጊስ በ16 ነጥብ ከአዳማ ከነማ በ3 ነጥቦች አንሶ ሁለተኛ ደረጃን ሲይዝ ደደቢት 3ኛ ደረጃውን ለሲዳማ ቡና አስረክቦ ወደ 4ና ደረጃ ወርዷል፡፡
የ7ኛ ሳምንት ጨዋታ ውጤቶች
ሀዋሳ ከነማ 1-2 አዳማ ከነማ
ቅዱስ ጊዮርጊስ 2-0 ደደቢት
ሀዲያ ሆሳእና 5-1 ወላይታ ድቻ
አርባምንጭ ከነማ 2-0 ኢትዮጵያ ቡና
ሲዳማ ቡና 1-0 መከላከያ
ድሬዳዋ ከነማ ከ ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ
ዳሽን ቢራ ከ ኤሌክትሪክ
የሊጉ ውድድር በቻን ምክንያት ለመጪዎቹ 45 ቀናት የሚቋረጥ ሲሆን የ8ኛ ሳምንት ጨዋታዎች የካቲት 5 ይደረጋሉ፡፡