ከፍተኛ ሊግ | ቡታጅራ ከተማ አዲስ አሰልጣኝ ቀጠረ

አሰልጣኝ አሥራት አባተ ከአሜሪካ መልስ ቡታጅራ ከተማን ለመረከብ ተስማምተዋል።

በሴቶች እግርኳስ ስኬታማ ጊዜያትን በማሳለፍ ከ2009 ጀምሮ ወደ ወንዶች ቡድን አሰልጣኝነት የተሸጋገሩት አሰልጣኝ አሥራት አባተ የ2011 የውድድር ዓመትን በቢሾፍቱ ከተማ ያሳለፉ ሲሆን ቡድኑን ለከፍተኛ ሊግ ለማሳደግ ተቃርበው በማጠቃለያ ውድድሩ ላይ ሳይሳካ ቀርቷል።

አሰልጣኙ በከፍተኛ ሊግ ምድብ ሐ ላለመውረድ ሲታገል የነበረውና በመጨረሻም የተረፈው ቡታጅራን ለማሰልጠን የተስማሙ ሲሆን በአዲሱ ቡድናቸው ጥሩ እግርኳስ የሚጫወት ተፎካካሪ ቡድን ለመስራት ጥረት እንደሚያደርጉ ለሶከር ኢትዮጵያ ተናግረዋል።


© ሶከር ኢትዮጵያ

በድረ-ገጻችን ላይ የሚወጡ ጽሁፎች ምንጭ ካልተጠቀሱ በቀር የሶከር ኢትዮጵያ ናቸው፡፡ እባክዎ መረጃዎቻችንን በሚጠቀሙበት ወቅት ምንጭ መጥቀስዎን አይዘንጉ፡፡