ወላይታ ድቻ አዲስ አሰልጣኝ ሾመ

ገብረክርስቶስ ቢራራ የወላይታ ድቻ አሰልጣኝ ሆነው ተሹመዋል።

ወላይታ ድቻ የውድድር ዓመቱን አጋማሽ በአሰልጣኝ አሸናፊ በቀለ እየተመራ ከነበረበት የመውረድ ስጋት አገግሞ የተሻለ ውጤት በማስመዝገብ በሊጉ መቆየቱን ማረጋገጡ ይታወቃል። ቡድኑ ከአሸናፊ ጋር በቀጣይ አብሮ ይቆያል ተብሎ ቢታሰብም አሰልጣኙ ምርጫቸውን የቀድሞ ክለባቸው አዳማ ከተማ አድርገዋል።

በዚህም ምክንያት አዲስ አሰልጣኝ የመቅጠር ግዴታ ውስጥ የገባው ወላይታ ድቻ ባሳለፍነው ሳምንት የአሰልጣኝ ቅጥር ማስታወቂያ ማውጣቱን ተከትሎ አስር አሰልጣኞች የስራ ልምዳቸውን በማስገባት ለውድድር ቀርበዋል። የክለቡ የቴክኒክ ኮሚቴ በወጣው መስፈርት መሠረት አነፃፅረው አሰልጣኝ ዘላለም ሽፈራው እና አሰልጣኝ ገብረክርስቶስ ቢራራን የመጨረሻ ዕጩ በማድረክ ለክለቡ የስራ አስፈፃሚ ቦርድ አቅርበዋል። በመጨረሻም የስራ አመራሩ ቦርድ በቀረቡለት ዕጩዎች ዙርያ ሰፊ ውይይት ካደረገ በኃላ አሰልጣኝ ገብረክርስቶስ ቢራራን ቀጣዩ የወላይታ ድቻ አሰልጣኙ አድርጎ ሾሟል።

አሰልጣኝ ገብረክርስቶስ ከዚህ ቀደም በዲላ ከተማ እና ደቡብ ፖሊስ መስራታቸው ይታወቃል።


© ሶከር ኢትዮጵያ

በድረ-ገጻችን ላይ የሚወጡ ጽሁፎች ምንጭ ካልተጠቀሱ በቀር የሶከር ኢትዮጵያ ናቸው፡፡ እባክዎ መረጃዎቻችንን በሚጠቀሙበት ወቅት ምንጭ መጥቀስዎን አይዘንጉ፡፡