ኢትዮጵያ የተካተተችበት ከ15 ዓመት በታች የሴካፋ ውድድር ድልድል ይፋ ሆኗል

በሴካፋ ታሪክ የመጀመርያ የሆነው ከ15 ዓመት በታች ወንዶች ውድድር በአስመራ ሲካሄድ የምድብ ድልድልም ወጥቷል።

የክፍለ አህጉሩ ሀገራትን የሚያሳትፈው ይህ ውድድር ከነሐሴ 9 እስከ 26 በኤርትራ መዲና አስመራ እንደሚካሄድ ሲገለፅ በሦስት ምድቦች 11 ሀገራት ተሳታፊ እንደሚሆኑ ይጠበቃል። ሊጀመር 8 ቀናት በቀሩበት ወቅት በውድድሩ ትሳተፍ አትሳተፍ ያልታወቀው ኢትዮጵያ በምድብ ድልድሉ ውስጥ ግን ተካታለች።

ምድብ ሀ
ኤርትራ፣ ኬንያ፣ ብሩንዲ፣ ሶማሊያ

ምድብ ለ
ዩጋንዳ፣ ሩዋንዳ፣ ኢትዮጵያ፣ ደቡብ ሱዳን

ምድብ ሐ
ታንዛኒያ፣ ሱዳን፣ ጅቡቲ

የኢትዮጵያ የምድብ ጨዋታዎች

ቅዳሜ ነሐሴ 10 ቀን 2011

ዩጋንዳ ከ ኢትዮጵያ (08:00)

ማክሰኞ ነሐሴ 13 ቀን 2011

ኢትዮጵያ ከ ሩዋንዳ (08:00)

ቅዳሜ ነሐሴ 17 ቀን 2011

ኢትዮጵያ ከ ደቡብ ሱዳን (10:30)


© ሶከር ኢትዮጵያ

በድረ-ገጻችን ላይ የሚወጡ ጽሁፎች ምንጭ ካልተጠቀሱ በቀር የሶከር ኢትዮጵያ ናቸው፡፡ እባክዎ መረጃዎቻችንን በሚጠቀሙበት ወቅት ምንጭ መጥቀስዎን አይዘንጉ፡፡