የሴካፋ ከ15 ዓመት በታች ውድድር ተጀመረ

ዛሬ በአስመራ ቺቾሮ ስታዲየም በተጀመረው የሴካፋ ከ 15 ዓመት በታች ዋንጫ ኬኒያ ስታሸንፍ አዘጋጅዋ ኤርትራ ሽንፈት አስታናግዳለች።

የውድድሩ መክፈቻ የነበረው ጨዋታ በኬንያ እና በሶማልያ የተካሄደ ጨዋታ ሲሆን ኬንያ በአንድርያስ ኦዲሃምቦ ፣ ጀምስ ጋቻጎ እና አንድሬው ዋሊአውላ ግቦች 3-1 በማሸነፍ ምድቧን መምራት ጀምራለች።

የመክፈቻው ሁለተኛ ጨዋታ በአዘጋጅዋ ኤርትራ እና ብሩንዲ መካከል የተካሄደ ሲሆን ብሩንዲ አዘጋጅዋን ሃገር 2-1 በመርታት የምድቡን ሁለተኛ ደረጃ ይዛለች።

ጨዋታዎቹ ነገም ሲቀጥሉ በስምንት ሰዓት ሃገራችን ኢትዮጵያ ዩጋንዳን ስትገጥም በአስር ከሰላላ ላይ ደግሞ ሩዋንዳና ደቡብ ሱዳን ይገናኛሉ።

ምድብ አንድ

1)ኬንያ ….. 3 – +2
2)ብሩንዲ…. 3 – +1
3)ሱዳን……. 0 – 0
4)ኤርትራ…. 0 – 1
5)ሶማሊያ…. 0 – 2