ዲዲዬ ጎሜስ ወደ ኢትዮጵያ ይመጣሉ

የቀድሞ የኢትዮጵያ ቡና አሰልጣኝ ዲዲዬ ጎሜስ ዳሮሳ ቀጣይ ሳምንት ወደ ኢትዮጵያ ይመጣሉ።

ባለፈው ዓመት አጋማሽ ከኢትዮጵያ ቡና ጋር ከተለያዩ በኋላ ወደ ጊኒ በማምራት ሆሮያን በአሰልጣኝነት ተረክበው ክለቡን የሊጉን ዋንጫ እንዲያነሳ ያስቻሉት እኚህ አሰልጣኝ ሁለት ኢትዮጵያውን አማካዮች ለመመልከት እና ከተጫዋቾቹ ንግግር ለማድረግ ነው ወደ ኢትዮጵያ የሚመጡት። በቆይታቸው የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድንን ጨዋታ ይመለከታሉ ተብለው የሚጠበቁት አሰልጣኙ እነማን ተጫዋቾች ላይ ፍላጎት እንዳሳዩ ያልታወቀ ሲሆን በኢትዮጵያ የቀናት ቆይታ ይኖራቸዋል ተብሎ ይጠበቃል።

በኢትዬጵያ ቆይታቸው ከቡናማዎቹ ጋር ጥሩ አጀማመር አድርገው ቀጣዩ የውድድር ዓመት ከተጀመረ በኋላ አጨዋወታቸው በቡድኑ ደጋፊዎች ያልተወደደላደቸው ፈረንሳዊው የ49 ዓመት አሰልጣኝ ከወራት በፊት ከሶከር ኢትዮጵያ ጋር ባደረጉት ቆይታ ኢትዮጵያውያን ተጫዋቾች ወደ ጊኒው ክለብ የመውሰድ ፍላጎት እንዳላቸው መግለፃቸው ይታወሳል።


© ሶከር ኢትዮጵያ

በድረ-ገጻችን ላይ የሚወጡ ጽሁፎች ምንጭ ካልተጠቀሱ በቀር የሶከር ኢትዮጵያ ናቸው፡፡ እባክዎ መረጃዎቻችንን በሚጠቀሙበት ወቅት ምንጭ መጥቀስዎን አይዘንጉ፡፡