አብዱልከሪም ኒኪማ አዲስ ክለብ አግኝቷል

ቡርኪናፏሳዊው የቀድሞ የቅዱስ ጊዮርጊስ ተጫዋች ካሪም ኒካማ ወደ አርሜንያ አቅንቷል።

ከአንድ ዓመት በፊት ወደ ኢትዮጵያ በመምጣት ከቅዱስ ጊዮርጊስ ጋር ጥሩ ዓመት አሳልፎ በበርካታ የክለቡ ደጋፊዎች ተወዳጅ የነበረው አማካዩ ከፈረሰኞቹ ጋር ከተለያየ በኃላ የተጠናቀቀውን የውድድር ዓመት ክለብ አልባ ሆኖ ቢቆይም ከአንድ ዓመት ቆይታ በኃላ ጋንድዛሳር ካፓን ለተባለ የአርሜንያ ክለብ ፊርማውን አኑሯል።

ተጫዋቹ በትላንትናው ዕለት ለአዲስ ክለቡ የመጀመርያው ጨዋታ ያደረገ ሲሆን በጨዋታውም ሎሪ ከተባለ ክለብ 1-1 አቻ ተለያይቷል።


© ሶከር ኢትዮጵያ

በድረ-ገጻችን ላይ የሚወጡ ጽሁፎች ምንጭ ካልተጠቀሱ በቀር የሶከር ኢትዮጵያ ናቸው፡፡ እባክዎ መረጃዎቻችንን በሚጠቀሙበት ወቅት ምንጭ መጥቀስዎን አይዘንጉ፡፡