ቶኪዮ 2020| የኢትዮጵያ እና ካሜሩን የመጀመርያ ጨዋታ የዛሬ ሳምንት ይደረጋል

በ2020 በጃፓኗ ቶኪዮ በሚካሄደው ኦሊምፒክ የሴቶች እግርኳስ ለመሳተፍ የሚካሄዱ የሁለተኛ ዙር የማጣርያ ጨዋታዎች በቀጣይ ሳምንት ይከናወናሉ።

ዩጋንዳን በድምር ውጤት 4-2 በመርታት ወደ ቀጣይ ዙር የተሻገረችው ኢትዮጵያ በሁለተኛው ዙር ከካሜሩን የምትጫወት ሲሆን በሜዳዋ የምታደርገውን ጨዋታ ሰኞ ነሐሴ 20 ለማከናወን እንደመረጠች የኢትዮጵያ እግርኳስ ፌዴሬሽን አስታውቋል። የመልሱ ጨዋታ ደግሞ ነሐሴ 28 እንዲደረግ ካሜሩን መምረጧን አያይዞ ገልጿል። ኢትዮጵያ ከነሐሴ 20-22 ያሉትን ቀናት የመምረጥ እድል ነበር የተሰጣት።)

ሉሲዎቹ ባሳለፍነው ቅዳሜ ወደ ኬንያ አምርታ የወዳጅነት ጨዋታ አድርጋ 3-2 ተሸንፋ መመለሷ የሚታወስ ሲሆን ትላንት አመሻሹን ጨዋታውን ወደሚያደርጉበት ባህር ዳር አቅንተዋል። የካሜሩን ሴቶች ብሔራዊ ቡድን በአንፃሩ ቅዳሜ አዲስ አበባ በመግባት እረፍት ካደረጉ በኋላ ወደ ባህር ዳር አምርተዋል።

በአጠቃላይ አምስት ዙሮች ባሉት በዚህ የማጣርያ ውድድር ኢትዮጵያ ተጋጣሚዋን አሸንፋ የምታልፍ ከሆነ በ3ኛው የማጣርያ ዉር የኮንጎ ዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ እና ኢኳቶርያል ጊኒን አሸናፊ ትገጥማለች።


© ሶከር ኢትዮጵያ

በድረ-ገጻችን ላይ የሚወጡ ጽሁፎች ምንጭ ካልተጠቀሱ በቀር የሶከር ኢትዮጵያ ናቸው፡፡ እባክዎ መረጃዎቻችንን በሚጠቀሙበት ወቅት ምንጭ መጥቀስዎን አይዘንጉ፡፡