ጋቶች ፓኖም ሌላኛውን የግብፅ ቡድን ተቀላቀለ

ባለፈው ሳምንት ከ ኤል ጎውና ጋር የተለያየው ኢትዮጵያዊው አማካይ ጋቶች ፓኖም ወደ ሌላው የግብፅ ክለብ በማምራት ሃራስ ኤል ሆዳድን ተቀላቅሏል።

ባለፈው ዓመት መጀመርያ መቐለ 70 እንደርታን ለቆ ወደ አዲስ አዳጊዎች ኤል ጎና በመቀላቀል ከክለቡ ጋር ጥሩ ዓመት ያሳለፈው ይህ ግዙፍ አማካይ ከክለቡ ጋር ቀሪ ውል እያለው በስምምነት ተለያይቶ ነው ኤል ሰውሐሎችን የተቀላቀለው።

ባለፈው ዓመት በኤል ጎና ቆይታው በአሰልጣኙ ቀዳሚ ተመራጭ የነበረው አማካዩ በቀጣይ የውድድር ዓመትም በአሰልጣኝ ታሪቅ ኤል አሽርይ ቀዳሚ ተመራጭ ይሆናል ተብሎ ይጠበቃል።

በአራት አጋጣሚ የአፍሪካ ውድድር ላይ የተሳተፈው አዲሱ የጋቶች ፓኖም ክለብ ከዚ በፊት በሁለት አጋጣሚ (በ2010 እና 2011) ወደ ኢትዮጵያ በመምጣት ከደደቢት እና ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ጋር መጫወቱ ይታወሳል።


© ሶከር ኢትዮጵያ

በድረ-ገጻችን ላይ የሚወጡ ጽሁፎች ምንጭ ካልተጠቀሱ በቀር የሶከር ኢትዮጵያ ናቸው፡፡ እባክዎ መረጃዎቻችንን በሚጠቀሙበት ወቅት ምንጭ መጥቀስዎን አይዘንጉ፡፡