ሴካፋ ከ15 ዓመት በታች | ኬንያ እና ብሩንዲ ሁለተኛ ተከታታይ ድል አስመዘገቡ

በኤርትራ አዘጋጅነት በብቸኝነት በቺቾሮ ስታዲየም እየተካሄደ የሚገኘው የሴካፋ ከ15 ዓመት በታች ዋንጫ ዛሬም ሲቀጥል ብሩንዲ እና ኬንያ አሸንፈዋል።

ቀድመው ጨዋታቸው ያካሄዱት ኬንያ እና ሱዳን ሲሆኑ በጨዋታውም ኬንያ በሰፊ ውጤት 4-0 አሸንፋለች። ኬንያ ከወዲሁም በመገናኛ ብዙሃን ለዋንጫ የታጨች ቡድን ሆናለች። ቀጥሎ የተካሄደው እና ጥሩ እንቅስቃሴ ታይቶበታል የተባለው የሶማሊያ እና የብሩንዲ ጨዋታ ሲሆን በጨዋታውም ብሩንዲ 2-1 አሸንፋለች።

ውድድሩ ነገም ሲቀጥል 8:00 ሰዓት ታንዛንያ ከ ዩጋንዳ በ10:30 ደግሞ ሃገራችን ኢትዮጵያ ከ ደቡብ ሱዳን ይገናኛሉ።


© ሶከር ኢትዮጵያ

በድረ-ገጻችን ላይ የሚወጡ ጽሁፎች ምንጭ ካልተጠቀሱ በቀር የሶከር ኢትዮጵያ ናቸው፡፡ እባክዎ መረጃዎቻችንን በሚጠቀሙበት ወቅት ምንጭ መጥቀስዎን አይዘንጉ፡፡