የብሔራዊ ቡድን ቀጣይ ጨዋታ የሚካሂድበት ስታድየም ታውቋል


የኢትዮጵያ ወንዶች ብሔራዊ ቡድን ለዓለም ዋንጫ ዝግጅት የሚያደርግበት እና ቀጣይ ጨዋታ የሚያካሄድበት ስታድየም ተለይቶ ታውቋል።

ከቀናት በፊት የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን ለዓለም ዋንጫ ማጣርያ ዝግጅት ተጫዋቾች መምረጡ ይታወሳል። አሁን ደግሞ ብሄራዊ ቡድኑ ለቀጣዩ ጨዋታ ቅድመ ዝግጅት የሚያደርግበት ከተማ እና ጨዋታ የሚያካሂድበት ስቴድየም ታውቋል። ባህር ዳር ከተማ ደግሞ የጨዋታው ምርጫ ሆናለች።

ነሃሴ 29 እና ጳጉሜ 3 ጨዋታዎቹን የሚያደርገው ብሔራዊ ቡድኑ ከአራት ቀን በኋላ ዝግጅቱን የሚጀምር ሲሆን አሰልጣኝ አብርሃም መብራቱም በተጫዋቾች ዝርዝር ከቡድኖቻቸው ጋር ጥሩ ዓመት ያሳለፉት ጀማል ጣሰው እና አንተነህ ተስፋዬን ከረጅም ጊዜ በኃላ ወደ ስብስባቸው ጠርተዋል። ኢትዮጵያ የመጀመርያው ጨዋታዋን ነሃሴ 29 በባህር ዳር ስታዲየም ማድረጓ ሲረጋገጥ ሁለተኛ ጨዋታዋም ወደ ሌሴቶ አምርታ ጨዋታዋን ታከናውናለች። ብሔራዊ ቡድኑ በአፍሪካ ዋንጫ ማጣርያ ከሌሶቶ ጋር በ2007 በተመሳሳይ በዚህ ስታዲየም አከናውኖ 2-1 ማሸነፉ የሚታወስ ነው። 

ከየሱፍ ሳላህ እና ዋሊድ አታ በኃላ ለትውልደ ኢትዮጵያውን ዕድል ያልሰጠው ብሄራዊ ቡድኑ ለአሚስ አስካር ፣ ዳንኤል ተሰማ እና ካሊድ ሙልጌታ ወደ ስብስቡ አካቷል። አሚን አስካር ከዚህ በፊትም ከናይጄርያ ጋር የዓለም ዋንጫ ማጣርያ ጨዋታ ለማድረግ በአሰልጣኝ ሰውነት ቢሻው ለብሄራዊ ቡድኑ ተጠርቶ በአንዳንድ የወረቀት ስራዎች ጨዋታ ሳያካሂድ ወደ ኖርዌይ መመለሱ ይታወሳል። ሌላው ወደ ብሄራዊ ቡድኑ ጥሪ የተደረገለት ግብ ጠባቂው ዳንኤል ተሰማ ሲሆን እሱም እንደ አሚን ከነርዌይ ሊግ የተገኘ ተጫዋች ነው። ሌላው ከጀርመን ወደ ብሄራዊ ጥሪ የተደረገለት የመስመር ተከላካዩ ካሊድ ሙሉጌታ ሲሆን ተጫዋቹ በ17 ዓመት በታች የጀርመን ብሄራዊ ቡድን ማልያ ለብሶም ተጫውቷል። ተጫዋቹ በዚ ሰዓት ክለብ አልባ ሲሆም ከዚ በፊት በሃኖቨር 96 ሁለት እና ዋሊድ ዛፓርሲች መጫወት ችሏል።


© ሶከር ኢትዮጵያ

በድረ-ገጻችን ላይ የሚወጡ ጽሁፎች ምንጭ ካልተጠቀሱ በቀር የሶከር ኢትዮጵያ ናቸው፡፡ እባክዎ መረጃዎቻችንን በሚጠቀሙበት ወቅት ምንጭ መጥቀስዎን አይዘንጉ፡፡