ቻን 2016፡ የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን የመጨረሻ የምድብ ጨዋታውን ነገ ደርጋል

 

በሩዋንዳ አስተናጋጅነት እየተካሄደ የሚገኘው የ2016 የአፍሪካ ሃገራት ዋንጫ ወደ ወሳኝ ምእራፍ ተሸጋግሯል፡፡ በምድብ 2 የምትገኘው ኢትዮጵያም ኮንጎን ተከትላ የማለፍ ጠባብ እድል ይዛ ነገ አንጎላን ትገጥማለች፡፡ የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን በኮንጎ 3-0 የተሸነፈበትን እና ከካሜሩን 0-0 የተለያየበትን ሁዬ ስታድየም ለቆ ወደ ኪጋሊ አማሆሮ ስታድየም ያቀና ሲሆን ነገ በ11፡00 ላይ አንጎላን የሚገጥም ይሆናል፡፡

ካሜሩንን ከገጠመው ቡድን ውስጥ ግብ ጠባቂው አቤል ማሞ ባጠመው የቁርጭምጭሚት ጉዳት ምክንያት የነገው ጨዋታ የሚያመልጠው ሲሆን ይድነቃቸው ኪዳኔ አልያም ደረጄ አለሙ የአቤልን ቦታ ተክተው ይሰለፋሉ፡፡ አማካዩ ጋቶች ፓኖምም በቁርጭምጭሚቱ ላይ ከደረሰበት ጉዳት አገግሞ ዛሬ ልምምድ ቢሰራም የነገውን ጨዋታ ለማድረግ ብቁ የመሆኑ ጉዳይ አጠራጣሪ ሆኗል፡፡ ከሁለቱ ተጫዋቾች ውጪ ሌላ የተጫዋች ጉዳት እንደሌለ ታውቋል፡፡

ከተጀመረ 8 ቀን ባስቆጠረው የቻን 2016 እስካሁን አስተናጋጇ ሩዋንዳ ፣ ኮትዲቯር ፣ ኮንጎ እና ዛምቢያ ወደ ሩብ ፍፃሜው ማለፋቸውን ሃገራት ናቸው፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *