ሴካፋ ከ15 ዓመት በታች| ኢትዮጵያ ከምድብ መሰናበቷን አረጋግጣለች

በኤርትራ አዘጋጅነት በመካሄድ ላይ የሚገኘውና አምስተኛ ቀኑ የያዘው የሴካፋ ከ15 ዓመት በታች ዋንጫ ዛሬም ሲቀጥል ታንዛኒያ እና ሩዋንዳ ተጋጣሚዎቻቸውን አሸንፈዋል። ኢትዮጵያ እና ደቡብ ሱዳንም ከምድቡ ተሰናባች መሆናቸውን አረጋግጠዋል።

በ08:00 የተካሄደው እና ሁለት ግምት ያልተሰጣቸው ቡድኖችን ያገናኘው የታኒዛንያ እና የደቡብ ሱዳን ጨዋታ በታንዛኒያ 6-0 አሸናፊነት ተጠናቋል። በዚህም ታንዛንያ በውድድሩ የመጀመርያ ድሏን ስታመዘግብ ነጥቧንም ሦስት በማድረስ የማለፍ ዕድልዋን አለምልማለች።

በዕለቱ ሁለተኛ በነበረው የኢትዮጵያ እና የሩዋንዳ ጨዋታ ሃገራችን ኢትዮጵያ 3-0 ተሸንፋለች። ይህን ተከትሎም ከሦስት ጨዋታዎች አንድ ነጥብ ብቻ የሰበሰበችው ኢትዮጵያ አንድ ጨዋታ እየቀራት ከምድቡ ተሰናባች መሆኗን አረጋግጣለች።

# ቡድን | ተጫ | ልዩነት | ነጥብ
1 ሩዋንዳ 2 (+6) 6
2 ዩጋንዳ 2 (+5) 6
3 ታንዛኒያ 2 (+4) 3
4 ኢትዮጵያ 3 (-6) 1
5 ደ/ሱዳን 3 (-9) 1

የውድድሩ 6ኛ ቀን ጨዋታዎች ነገ ሲቀጥሉ በ8:00 ሶማሊያ ከ ሱዳን ሲጫወቱ በ10:30 አስተናጋጇ ኤርትራ የምድቡ ጠንካራ ቡድን ኬንያን ትገጥማለች።


© ሶከር ኢትዮጵያ

በድረ-ገጻችን ላይ የሚወጡ ጽሁፎች ምንጭ ካልተጠቀሱ በቀር የሶከር ኢትዮጵያ ናቸው፡፡ እባክዎ መረጃዎቻችንን በሚጠቀሙበት ወቅት ምንጭ መጥቀስዎን አይዘንጉ፡፡