ኢትዮጵያ ቡና ተከላካይ ለማስፈረም ተስማምቷል

ዘግየት ብለው ወደ ተጨዋቾች ዝውውር የገቡት ኢትዮጵያ ቡናዎች አምስተኛ ተጨዋቻቸውን ለማስፈረም ተስማምተዋል።

ከጣና ሞገዶቹ ጋር ጥሩ ጊዜ ያሳለፈው ወንድሜነህ ደረጄ ከሱሉልታ ከተማ ወደ ባህር ዳር ከተማ በ2009 የተዘዋወረ ሲሆን ቡድኑ ወደ ኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ሲያድግ ወሳኝ ግልጋሎት አበርክቷል። ባሳለፍነው የውድድር ዓመትም በቋሚነት ከአቤል ውዱ ጋር ጠንካራ ጥምረት ፈጥሮ ዓመቱን ሲቋጭ በብሔራዊ ቡድንም ጥሪ ደርሶታል።

ይህ የተከላካይ መስመር ተጫዋች ከተለያዩ ክለቦች ጋር ስሙ ቢያያዝም ቡናማዎቹን ለሁለት ዓመት ለማገልገል መስማማቱ ተረጋግጧል።


© ሶከር ኢትዮጵያ

በድረ-ገጻችን ላይ የሚወጡ ጽሁፎች ምንጭ ካልተጠቀሱ በቀር የሶከር ኢትዮጵያ ናቸው፡፡ እባክዎ መረጃዎቻችንን በሚጠቀሙበት ወቅት ምንጭ መጥቀስዎን አይዘንጉ፡፡