መከላከያ የአጥቂ መስመር ተጫዋቹን የክለቡ አምስተኛ ፈራሚ አደረገ

አሰልጣኝ ዘላለም ሽፈራው ለቀጣይ ዓመት መከላከያን ለማጠናከር በማሰብ በዝውውሩ እየተንቀሳቀሱ ሲሆን ዛሬ ደግሞ ፈጣኑ የመስመር አጥቂ ሐብታሙ ገዛኸኝን አስፈርመዋል።

በደቡብ ፖሊስ እና ሲዳማ ቡና መጫወት የቻለው የመስመር አጥቂው በዓመቱ መጀመርያ በኦሊምፒክ ብሄራዊ ቡድን ተሰልፎ መጫወቱ ሲታወስ ቡድኑ ሲዳማ ቡና ሁለተኛ ደረጃ ይዞ እንዲያጠናቅቅ ትልቅ ድርሻ ከተወጡ ተጫዋቾች መካከል አንዱ ነበር። ከመስመር እየተነሳ በሚፈጥራቸው አደገኛ የጎል አጋጣሚዎች የየሚታወቀው ሐብታሙ ወሳኝ ግቦችም ማስቆጠር ችሏል።

ከዚህ ቀደም ታላቅ ወንድሙ ባዬ ገዛኸኝ ወደተጫወተበት ቡድን ያመራው ሐብታሙን ጨምሮ ግብጠባቂው ምንተስኖት አሎ ፣ አስናቀ ሞገስ እና ነስረዲን ኃይሉ ለመከላከያ ፊርማቸውን አኑረዋል።


© ሶከር ኢትዮጵያ