ኳታር 2022 | ሁለት ተጫዋቾች ከነገው ጨዋታ ውጪ ሆኑ

በ2022 በኳታር አዘጋጅነት ለሚካሄደው የዓለም ዋንጫ ቅድመ ማጣሪያ ከሌሶቶ ጋር ነገ ነሐሴ 29 በባህር ዳር ስታዲየም የሚጫወቱት ዋሊያዎቹ ግብጠባቂው ምንተስኖት አሎ እና አማኑኤል ዮሐንስን እንደማይጠቀሙ ተረጋግጧል።

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ዋና አሰልጣኝ አብርሀም መብራቱ የነገውን ጨዋታ አስመልክቶ በዩኒሰን ሆቴል ለጋዜጠኞች በሰጡት መግለጫ ” ግብጠባቂው ምንተስኖት አሎ እና አማካዩ አማኑኤል ዮሐንስ ብዙም የከፋ ጉዳት አላጋጠማቸውም። ሆኖም ለነገው ጨዋታ እንደማይደርሱ የህክምና ቡድኑ ማረጋገጫ ሰጥቶናል። ለነገው ጨዋታ አይድረሱ እንጂ ለመልሱ ጨዋታ ይደርሳሉ ብለን እናስባለን” ብለዋል።

በቀጣይ በነገው ጨዋታ ዙርያ አሰልጣኝ አብርሀም መብራቱ እና የቡድኑ አምበል ሽመልስ በቀለ የሰጡትን መግለጫ ዘገባችን ይዘን የምንቀርብ ይሆናል።


© ሶከር ኢትዮጵያ