በሴካፋ ከ20 ዓመት በታች ውድድር ኢትዮጵያ ተጋጣሚዎቿን አውቃለች

ዩጋንዳ ለምታዘጋጀው የሴካፋ ከ 20 ዓመት በታች የምድብ ድልድል ይፋ ሆኗል።

በውድድሩ ተሳታፊ ለመሆን በዝግጅት ላይ የምትገኘው ኢትዮጵያ በምድብ ሁለት ከኬንያ ፣ ታንዛንያ እና ዛንዚባር የተመደበች ሲሆን በአሰልጣኝ ዮሴፍ ተስፋዬ እየተመራ ዝግጅት እያደረገ የሚገኘው ቡድኑ ከሰባት ቀናት በኋላ በሚጀምረው ውድድር ላይ ለመሳተፍ ከቀናት በኃላ ወደ ዩጋንዳ ያመራል።

ባለፈው ማክሰኞ ኒኮላስ ሙሶንዬን ጨምሮ በርካታ የሴካፋ የበላይ ሃላፊዎች የዩጋንዳን ዝግጅት መመልከታቸው የሚታወስ ሲሆን ውድድሩ በአስራ አንድ ሀገራት መካከል ስታር ታይምስን ጨምሮ በሦስት ስታዲየሞች ይካሄዳል።

የምድብ ድልድሉ ይህንን ይመስላል፡-

ምድብ አንድ፡ ዩጋንዳ፣ ኤርትራ፣ ጅቡቲ፣ ሱዳን

ምድብ ሁለት፡ ኬንያ፣ ኢትዮጵያ፣ ዛንዚባር፣ ታንዛንያ

ምድብ ሦስት፡ ብሩንዲ፣ ደቡብ ሱዳን፣ ሶማሊያ


© ሶከር ኢትዮጵያ