ሀዋሳ ከተማ ሁለት ተጫዋቾችን አስፈረመ

ሀዋሳ ከተማ ግብ ጠባቂው ሐብቴ ከድር እና አማካዩ ዘላለም ኢሳይያስን አስፈርሟል፡፡

ሐብቴ ከድር ከሀላባ ከተማ የእግር ኳስ ህይወቱን ጅማሮ አደርጎ በሀዲያ ሆሳዕና እና አውስኮድ ተጫውቶ አሳልፏል፡፡ በ2011 የውድድር ዘመን በደቡብ ፓሊስ ቆይታ ያደረገው ይህ ግብ ጠባቂ በክለቡ ጥሩ ጊዜን አሳልፎ በሁለት ዓመታት ውል ማረፊያውን ሀዋሳ ከተማ አድርጎል፡፡

ሌላኛው ሀዋሳን በሁለት አመት መቀላቀል የቻለው አማካዩ ዘላለም ኢሳይያስ ነው፡፡ በወልቂጤ ከተማ ክለብ ውስጥ እግር ኳስን የጀመረው አማካዩ በደቡብ ፖሊስ ከዚያም በድሬዳዋ ከተማ ቆይታ አድርጎ በ2011 ወደ ደቡብ ፖሊስ በመመለስ በግሉ ስኬታማ ጊዜ ማሳለፍ ችሏል። ተጫዋቹ በቅርቡ ወደ ወላይታ ድቻ ለማምራት ቅድመ ስምምነት ፈፅሞ የነበረ ቢሆንም ፊርማውን ሳያኖር ወደ ሀዋሳ አምርቷል።

በተያያዘ የክለቡ ዜና ከነባር ተጫዋቾች መካከል አስራ አንድ ዓመታትን በሀዋሳ ያሳለፈው ተከላካዩ አዲስዓለም ተስፋዬ፣ ዳንኤል ደርቤ እና አስጨናቂ ሉቃስ በክለቡ ለመቆየት ፊርማቸውን አኑረዋል።


© ሶከር ኢትዮጵያ