ፍሊፕ ኦቮኖ በመቐለ ውሉን አራዘመ

በሊግ ቻምፒዮኖቹ ጋር የመቆየቱ ነገር ጥያቄ ምልክት ውስጥ ገብቶ የነበው ፊሊፕ ኦቮኖ ከክለቡ ጋር ለመቆየት ተስማምቷል።

ኢኳቶርያል ጊኒያዊው ግብ ጠባቂ ከክለቡ ጋር የነበረው የሁለት ዓመት ውል መጠናቀቁን ተከትሎ ስሙ ከበርካታ ክለቦች ጋር ሲያያዝ የቆየ ሲሆን ተጫዋቹም ባሳለፈው ወር መጨረሻ ላይ ከሃገር ውስጥ ክለቦች የዝውውር ጥያቄ እንደቀረበለት ገልጾ እንደነበር ይታወሳል። ተጫዋቹ በመጨረሻም ውሉን ለማራዘም እና ለሦስተኛ የውድድር ዓመት በክለቡ ለመቆየት ተስማምቷል።

ከባለፈው ወር ጀምሮ የበርካታ ነባር ተጫዋቾቻቸው ውል በማራዘም የሚገኙት መቐለዎች ለማሊያውያኑ ሙሳ ካማራ እና ማማዱ ሲምፓራ የሙከራ ዕድል መስጠታቸውም ይታወቃል።


© ሶከር ኢትዮጵያ