የሱፍ ሳላህ አዲስ ክለብ ተቀላቅሏል

ኢትዮጵያዊው የመስመር አማካይ የሱፍ ሳላህ ፋርስታ ለተባለ የስዊድን ክለብ ፊርማውን አኑሯል።

ከኢትዮጵያውያን ቤተሰቦች በስዊድን ሃገር ተወልዶ ለኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድንም መጫወት የቻለው ፈጣኑ የመስመር አማካይ የሱፍ ሳላህ ባለፈው የውድድር ዓመት በሦስተኛ የሊግ እርከን ለሚጫወተው ቫሳሉንድስ ለተባለ ቡድን ሲጫወት የቆየ ሲሆን አሁን ደግሞ ፋርስታ ለተባለው የስድስተኛ ዲቪዝዮን ቡድን ፌርማውን አኑሯል።

የ35 ዓመቱ የሱፍ በእግር ኳስ ህይወቱ ለ11 ክለቦች የተጫወተ ሲሆን ከትውልድ ከተማው ክለብ ሶሊና የአልስቨንስካን ጋር የሊጉን ጨምሮ ሦስት ዋንጫዎች አንስቷል። በኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን ቆይታውም በ12 ጨዋታዎች ተሰልፎ ሁለት ግቦች ማስቆጠር ችሏል።


© ሶከር ኢትዮጵያ