ከፍተኛ ሊግ | ጌዴኦ ዲላ ሦስት ተጨማሪ ተጫዋቾችን አስፈረመ

አሰልጣኝ ደረጀ በላይን በዋና አሰልጣኝነት የቀጠረው ጌዲኦ ዲላ አዳዲስ ተጫዋቾችን ወደ ቡድኑ መቀላቀሉን ቀጥሎ የሦስት ተጫዋቾችን ዝውውር አጠናቋል።

ታደሰ ያለው (ፎቶ-መሐል) ለዲላ ከፈረሙት መካከል ነው። ግብ ጠባቂው ከዚህ ቀደም በድሬዳዋ ፖሊስ፣ ፌዴራል ፖሊስ፣ ንፋስ ስልክ እና የካ ክፍለ ከተማ ተጫውቷል።

ምትኩ ጌታቸው (ፎቶ-ቀኝ) ሌላው አዲስ ተጫዋች ነው። በመስመር እና በአጥቂነት የሚጫወተው ምትኩ በአርሲ ነገሌ እና በቡታጅራ የተጫወተ ሲሆን በ2011 የውድድር ዓመት በአርሲ ነገሌ ቡድኑን በአምበልነት እየመራ ጥሩ ጊዜ ከማሳለፉ በተጨማሪ የቡድኑ ከፍተኛ ጎል አስቆጣሪ ነበር።

ታምሩ ባልቻ (ፎቶ – ግራ) ሌላው ወደ ዲላ ያመራ ተጫዋች ሆኗል። የፊት መስመር ተሰላፊው ታምሩ በየካ ክፍለ ከተማ፣ ኢትዮጵያ መድን እና ኢኮስኮ ተጫውቶ ያሳለፈ ሲሆን በመድን አብረውት ከሰሩት አሰልጣኝ ደረጄ በላይ ጋር በዲላ በድጋሚ የሚገናኝ ይሆናል።

ጌዴኦ ዲላ እስካሁን ስምንት ተጫዋቾችን ወደ ቡድኑ ሲቀላቅል የስድስት ነባሮችን ውል ማራዘምም ችሏል።


© ሶከር ኢትዮጵያ