ወላይታ ድቻ የቀድሞ ግብ ጠባቂውን በድጋሚ አስፈረመ

ወላይታ ድቻ የቀድሞ ግብ ጠባቂው መክብብ ደገፉን ከአራት ዓመታት በኃላ በድጋሚ አስፈርሞታል፡፡

በ2005 በወላይታ ድቻ የእግርኳስ ህይወቱን የጀመረው መክብብ በወላይታ ድቻ እስከ 2008 ድረስ የተጫወተ ሲሆን ክለቡ ወደ ፕሪምየር ሊግ ሲያድግ የብሔራዊ ሊግ ኮከብ ጎል ጠባቂ ሆኖ ከመመረጡ ባሻገር በቀጣዩ ዓመት በፕሪምየር ሊጉ ድንቅ አቋሙን ማሳየት ችሎ ነበር። ድቻን ከለቀቀ በኋላ ለሀዋሳ ከተማ፣ አዳማ ከተማ እንዲሁም በከፍተኛ ሊጉ ሀምበሪቾ መጫወት የቻለ ሲሆን ዐምና ደግሞ በደቡብ ፖሊስ ቆይታ አድርጓል፡፡

በመጀመሪያው ዙር ከቴሴራ ጋር በተያያዘ የመጫወት ዕድል ያላገኘውና በሁለተኛው ዙር ተሰልፎ መጫወት የቻለው ይህ ግብ ጠባቂ በደቡብ ፖሊስ አብሮ ካሳለፈው አሰልጣኝ ገብረክርስቶስ ቢራራ ጋር በድጋሚ ይገናኛል። ታሪክ ጌትነት ክለቡን የለቀቀ በመሆኑም ከሌላኛው ግብ ጠባቂ መኳንንት አሸናፊ እና ከሁለት ታዳጊ ግብ ጠባቂዎች ጋር ለቋሚነት ይፎካከራል፡፡


© ሶከር ኢትዮጵያ