ለሴካፋ ከ20 ዓመት በታች ውድድር ሁለት ኢትዮጵያዊያን ዳኞች ተመርጠዋል

የሴካፋ ከ20 ዓመት በታች ዋንጫ በዩጋንዳ አስተናጋጅነት ዕሁድ ሲጀመር አንድ ዋና እና አንድ ረዳት ዳኞች ከኢትዮጵያ ተመርጠዋል። 

በዚህ ውድድር ላይ ሀገራችን ኢትዮጵያ ከብሔራዊ ቡድን ተሳትፎዋ ባለፈም ሁለት ዳኞችን ለዚህ ውድድር አስመርጣለች፡፡ በቅርቡ በኤርትራ አስተናጋጅነት ተዘጋጅቶ በነበረው ከ17 ዓመት በታች ዋንጫ ላይ መርቶ የነበረው ኢንተርናሽናል ዳኛ ለሚ ንጉሴ በድጋሚ በሴካፋ ከ20 ዓመት በታችን እንዲመራ የተመረጠ ሲሆን ኢንተርናሽናል ረዳት ዳኛ በላቸው ይታየው ሌላኛው በውድድሩ ላይ በዳኝነት እንዲመራ የተመረጠ ሆኗል፡፡


© ሶከር ኢትዮጵያ