ሰማያዊዎቹ የቀድሞ አሰልጣኛቸውን ለመቅጠር ተስማምተዋል

የፎርማቱን መቀየር ተከትሎ በሊጉ መቆየት የቻሉት ደደቢቶች የቀድሞ አሰልጣኛቸው ጌታቸው ዳዊትን አዲስ አሰልጣኝ አድርገው ለመቅጠር ተስማምተዋል።

ቀጣይ ዓመት በአዲስ ባለቤት ወደ ውድድር የሚመለሱት ሰማያዊዎቹ በቀጣይ ጥቂት ቀናት ወደ ዝውውሩ ይገባሉ ተብሎ ሲጠበቅ ከአሰልጣኝ ጌታቸው ዳዊት ጋርም በይፋ ይፈራረማሉ ተብሎ ይጠበቃል። ከዚ በፊት በ2008 ሰማያዊዎቹን የመሩት አሰልጣኝ ጌታቸው ወልዋሎ፣ መቐለ እና አክሱም ከተማን ማሰልጠናቸው ሲታወስ በ2009 መቐለ 70 እንደርታን ወደ ፕሪምየር ሊግ አሳድገው የ2010 የውድድር ዓመት ከመጀመሩ ጥቂት ሳምንታት በፊት በዓዲግራት መስቀል ዋንጫ በተከሰቱ ጉዳዮች ከቡድኑ ጋር መለያየታቸው ይታወሳል።

ቀደም ብለው በመሰቦ ስር እንደሚቀጥሉ የገለፁት ደደቢቶች ባለፈው ዓመት የነበረባቸው የፋይናንስ ችግር እንደተቀረፈላቸው አስቀድመው መግለፃቸው ሲታወስ ቡድኑ ከዚህ ቀደም ወደሚታወቁበት ታዳጊዎችን ማብቃት ላይ እንደሚሰሩም ከክለቡ ለማወቅ ተችሏል።


© ሶከር ኢትዮጵያ