ቻን 2020| ዋልያዎቹ ልምምዳቸውን ቀጥለዋል

በአፍሪካ ሀገራት ዋንጫ (ቻን) ማጣርያ ከሩዋንዳ ጋር የሚጫወተው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ሁለት ተጫዋቾችን በመቀላቀል በመቀለ ልምምዱን ቀጥሏል።

ቡድኑ በመቐለ በጥሩ ሁኔታ ልምምዱን የቀጠለ ሲሆን ከነበሩት ተጫዋቾች በተጨማሪ ባለፈው ሳምንት የሰርግ ሥነ-ስርዓታቸው በማካሄዳቸው ከብሔራዊ ቡድኑ ጋር ዝግጅት ያልጀመሩት አሕመድ ረሺድ እና ያሬድ ባየህ ትናንት ብሄራዊ ቡድኑ ተቀላቅለው ልምምድ ጀምረዋል።

ዋልያዎቹ ከአንድ መርሐ ግብር በስተቀር ሙሉ ልምምዳቸውን በዋናው የትግራይ ስታዲየም ሲያደርጉ የቆዩ ሲሆን ዋና አሰልጣኙ ባቀረቡት ጥያቄ መሰረትም የስታዲየሙ ሳር እንዲቀነስ ተደርጓል። በእስካሁኑ የመቐለ ቆይታቸው በአብዛኛው የአካል ብቃት ልምምዶች ላይ ያተኮሩት አሰልጣኝ አብርሃም መብራቱ ብሔራዊ ቡድኑን የተሻለ የአካል ብቃት ካላቸው ሩዋንዳዎች ጋር ለማመጣጠን ያለመ የሚመስል ልምምድ እየከወኑም ይገኛሉ።


© ሶከር ኢትዮጵያ