ሀዋሳ ከተማ ብርሀኑ በቀለን አስፈርሟል

ወደ ወልቂጤ ከተማ ለማምራት ቅድመ ስምምነት ፈፅሞ የነበረው ሁለገቡ ተጫዋች ብርሀኑ በቀለ ለሀዋሳ ከተማ በዛሬው ዕለት ፊርማውን አኑሯል፡፡

በወንዶ ገነት እግር ኳስን የጀመረው እና በቀኝ ተከላካይ፣ በመስመር አጥቂ እና በአጥቂ ቦታ ላይ መጫወት የሚችለው ብርሀኑ በሲዳማ ቡና የታዳጊ ቡድን እና በሻሸመኔ ከተማ ተጫውቶ ያሳለፈ ሲሆን በተለይ ባለፉት ሦስት ዓመታት በደቡብ ፖሊስ ጥሩ ቆይታን አድርጓል፡፡

ብርሀኑ ከሳምንታት በፊት ወደ ወልቂጤ ከተማ ለማምራት ስምምነት ፈፅሞ የነበረው ቢሆንም በይፋ ሳይፈራረም ማረፊያውን ሀዋሳ ከተማ አድርጓል፡፡


© ሶከር ኢትዮጵያ