የሴቶች ዝውውር | ምርቃት ፈለቀ ወደ አዳማ ከተማ አምርታለች

ከዚህ ቀደም ሁለት ተጫዋቾችን ማስፈረማቸውን ያረጋገጡት የዐምናው የአንደኛ ዲቪዚዮን አሸናፊ አዳማ ከተማዎች በዛሬው ዕለት ምርቃት ፈለቀን በእጃቸው ማስገባታቸውን አረጋግጠዋል፡፡

ለአዲሱ የውድድር ዘመን መጠነኛ ለውጦችን በማድረግ የዐምናውን ክብራቸውን ለማስጠበቅ እየተንቀሳቀሱ የሚገኙት አዳማዎች ወደ ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ለማምራት ከጫፍ ደርሳ የነበረችው ምርቃት ፈለቀን በስተመጨረሻም ሊያስፈርሙ ችለዋል፡፡ በኢትዮጵያ ሴቶች እግርኳስ በቅርብ አመታት ከታዩ ባለተሰጥኦ የአጥቂ ስፍራ ተጫዋቾች መካከል አንዷ የሆነችው ምርቃት ባለፉት ዓመታት በአሰልጣኝ ዮሴፍ ገ/ወልድ በሚመራው የሀዋሳ ከተማ ቡድን ውስጥ ጎልታ መውጣት ከመቻሏም በላይ በኢትዮጵያ ሴቶች ብሔራዊ ቡድን ላይም ጭምር ተስፋ ሰጪ እንቅስቃሴን ማሳየት ችላለች፡፡

ዐምና በአስፈሪ የአጥቂ ስፍራ ጥምረታቸው የተቃራኒ ቡድኖች ላይ ግብ ሲያዘንቡ የከረመት አዳማዎች በዘንድሮ ዓመትም በአዲስ መልኩ ጠንካራ የአጥቂ ጥምረት ይዘው ይቀርባሉ ተብሎ ይጠበቃሉ


© ሶከር ኢትዮጵያ