ሴቶች ዝውውር | ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ተጨማሪ ተጫዋች ወደ ቡድኑ ቀላቅሏል

ትላንት የስድስት ተጨዋቾችን ዝውውር ያጠናቀቁት ኢትዮጵያ ንግድ ባንኮች ዛሬ ረፋድ አንድ ተጨማሪ ተጫዋች አስፈርመዋል።

ቡድኑ ያስፈረመው ሰባተኛ ተጨዋች ሜላት ደመቀ ናት። ከዚህ ቀደም በአዳማ ከተማ ቆይታ ያደረገችው ሜላት ባሳለፍነው የውድድር ዓመት ከአዲስ አበባ ከተማ ጋር ጥሩ ጊዜ ማሳለፏ ይታወቃል። ይህቺ የአማካይ መስመር ተጫዋች በተለያዩ የእድሜ እርከኖች የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድንን ማገልገሏም ይታወሳል።

ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሜላትን ጨምሮ የሰባት ተጨዋቾችን ዝውውር ሲያጠናቅቅ የአራት ነባር ተጨዋቾችን ውል ማደሱ ይታወሳል። ቡድኑ ምናልባት ከዚህ በኋላ ሶስት ተጨዋቾችን ወደ ቡድኑ ይቀላቅላል ተብሎ ይጠበቃል።


© ሶከር ኢትዮጵያ