የቀድሞ የፈረሰኞቹ አሰልጣኝ አዲስ ሹመት አግኝተዋል

ባለፈው ዓመት ከፈረሰኞቹ ጋር ቆይታ የነበራቸው ፖርቹጋላዊወረ ወጣት አሰልጣኝ ማኑኤል ቫዝ ፒንቶ በፖርቹጋል ዋናው ሊግ (ፕሪሜራ ሊጋ) የሚሳተፈው ፋማሊሳኦ የተስፋ ቡድንን ለማሰልጠን ተስማሙ።

ባለፈው ዓመት በሊጋ-ፕሮ ፓኮስ ደፌሬራን ተከትለው ወደ ዋናው የፖርቹጋል ሊግ ያደጉት እና ፋማሊሳኦዎች ከዚህ ቀደም ለሠባት ጊዜያት በፖርቹጋል ዋናው ሊግ ተሳትፈዋል።

ቅዱስ ጊዮርጊስን ጨምሮ በአንጎላዎቹ ሪክሬቲቮ ዲ ካላ እና ሪክሬቲቮ ሊ ቦሎ ያሰለጠኑት ፖርቹጋላዊው አሰልጣኝ ወደ አፍሪካ ከመምጣታቸው በፊት በአሁኑ ክለባቸው በቴክኒካል ዳይሬክተርነት ጨምሮ በተለያዩ የቴክኒክ ቦታዎች ላይ መስራት ችለዋል። በቀጣይ ዓመትም ከ23 ዓመት በታች ቡድን ይዘው በፖርቹጋል ተስፋ ሊግ (Liga Revelação) የሚሳተፉ ይሆናል።

በሌላ ዜና የአሰልጣኝ ማኑኤል ቫዝ ፒንቶ ልጅ ጉልሄርሜ ቫዝ ፒንቶ ሲዲ ቶንዴላ የተሰኘ ሀገሪቱን ከ17 ዓመት በታች ቡድንን ተቀላቅሏል።


© ሶከር ኢትዮጵያ