ወላይታ ድቻ አምስት ተጫዋቾችን ወደ ዋናው ቡድኑ አሳድጓል


ወላይታ ድቻ የኢትዮጵያ ከ20 ዓመት በታች ፕሪምየር ሊግ ቻምፒዮን ከሆነው ስብስብ ውስጥ ተስፈኛ እንቅስቃሴ ያደረጉ አምስት ወጣቶችን ወደ ዋናው ቡድን አሳድጓል፡፡

ካደጉት ተጫዋቾችን መካከል ተከላካዩ አዛርያስ አቤል፣ ፈጣኑ አጥቂ ታምራት ስላስ እና አማካዩ አበባው አጪሶ ለሴካፋ ከ20 ዓመት በታች ሀገራችንን ለመወከል ተካተው የሚገኙ ሲሆን አማካዩ መሳይ ኒኮላ እንዲሁም ተከላካዩ ግሩም ሚሊዮን የዋናው ቡድን አባል የሆኑ ተጫዋቾች ሆነዋል፡፡

እስከ አሁን በዝውውር ሂደቱ ይግረማቸው ተስፋዬ፣ ነጋሽ ታደሰ፣ ተመስገን ታምራት እና መክብብ ደገፉን ወደ ቡድኑ የቀላቀለው ወላይታ ድቻ የቅድመ ውድድር ዝግጅቱን ከትላንት በስቲያ በቦዲቲ ጀምሯል፡፡


© ሶከር ኢትዮጵያ