ደቡብ ፖሊስ ተጨማሪ ተጫዋቾችን አስፈርሟል


ደቡብ ፖሊስ አመሻሹን ተጨማሪ ሁለት ተጫዋቾችን በማስፈረም የአዳዲስ ተጫዋቾችን ቁጥር ወደ ዘጠኝ ከፍ አድርጓል፡፡

የአጥቂ ስፍራ ተጫዋቹ ሙሉጌታ ረጋሳ ወደ ደቡብ ፖሊስ ያመራ ተጫዋች ሆኗል፡፡ የቀድሞው የመከላከያ፣ ወልዲያ፣ መቐለ እና ወልቂጤ የአጥቂ ስፍራ ተጫዋች ዐምና በከፍተኛ ሊጉ ክለብ አክሱም ከተማ ጥሩ ጊዜ ካሳለፈ በኃላ በድጋሚ ወደ ፕሪምየር ሊጉ በመመለስ ለደቡብ ፖሊስ መፈረም ችሏል፡፡

ወጣቱ የአጥቂ ስፍራ ተጫዋች ሐብታለም ታፈሰ ዘጠነኛው የቢጫ ለባሾቹ ፈራሚ ሆኗል። በ2010 የኢትዮጵያ ከ20 ዓመት በታች ፕሪምየር ሊግ ኮከብ ተጫዋች ሆኖ ከተመረጠ በኋላ ዐምና ወደ ወላይታ ድቻ ዋናው ቡድን ያደረገው ሐብታለም ማረፊያውን የተመስገን ዳናውን ክለብ አድርጓል፡፡

ደቡብ ፖሊስ በቀጣዮቹ ቀናት ጥቂት ዝውውርን ከፈፀመ በኋላ በቀጣዩ ሳምንት ማክሰኞ ወደ ቅድመ ውድድር ዝግጅት የሚገባ ይሆናል፡፡


© ሶከር ኢትዮጵያ