አማኑኤል ገብረሚካኤል ከምዓም አናብስት ጋር ለመቆየት ተስማምቷል

ስሙ ከበርካታ ክለቦች ጋር ሲያያዝ የቆየው አማኑኤል ገብረሚካኤል በመጨረሻም ከመቐለ ጋር ለመቆየት ተስማምቷል።

ከመቐለ 70 እንደርታ ጋር የነበረውን የሁለት ዓመት ውል መጠናቀቁን ተከትሎ ስሙ ከግብፅ ክለቦች ጨምሮ ከበርካታ ክለቦች ሲያያዝ የቆየው የመስመር አማካዩ አማኑኤል ለቀጣይ ሁለት ዓመታት ከመቐለ ጋር ለመቆየት ነው የተስማማው።

ከዳሽን ቢራ ሁለተኛ ቡድን አድጎ ለሰሜን ሸዋ ደብረብርሃን እና መቐለ የተጫወተው ተጫዋቹ በዚህ ዓመት ከክለቡ ጋር አራተኛ የውድድር ዓመቱን ያሳልፋል።


© ሶከር ኢትዮጵያ