ሴካፋ U-20 | ታንዛንያ እና ኬንያ ተጋጣሚዎቻቸውን በሰፊ ውጤት ረምርመዋል

ቅዳሜ የተጀመረው የሴካፋ ከ20 ዓመት በታች ዋንጫ እሁድም ሲቀጥል ታንዛንያ ኢትዮጵያን፤ ኬንያ ደግሞ ዛንዚባርን በሰፊ ውጤት አሸንፈዋል።

በንጅሩ ስታዲየም ቀድመው ጨዋታቸውን ያካሄዱት ኢትዮጵያ እና ታንዛንያ ሲሆኑ ታንዛንያም በአንድሪው አልበርት ሃትሪክ እና በካልቢን ጆን አንድ ጎል 4-0 አሸንፋለች።

የዚህ ዕለት ሁለተኛ ጨዋታ የነበረው በኬንያ እና ዛንዚባር መካከል የተካሄደው ሲሆን ውጤቱም ኬንያ 5-0 አሸንፋለች። ሲድኒ ሎካሌ የተባለ ተጫዋችም አራት ግቦች አስቆጥሯል።

ውድድሩ ሰኞም ሲቀጥል ኤርትራ ከ ሱዳን፤ ዩጋንዳ ከ ጅቡቲ ይገናኛሉ።


© ሶከር ኢትዮጵያ