ደቡብ ፖሊስ ተጨማሪ ተጫዋች አስፈረመ

ደቡብ ፖሊስ የአጥቂ አማካዩ ቴዲ ታደሰን በአንድ ዓመት ውል አስፈርሟል፡፡

ቴዲ በባህርዳር ከተማ የእግር ኳስ ህይወቱን ከጀመረ በኋላ በጣና ሞገደኞቹ ቤት አራት ዓመታትን አሳልፎ በገጠመው መጠነኛ ጉዳት ከሜዳ ቢርቅም ከ2009 ጀምሮ ግን ወደ እግር ኳስ ተመልሶ አስደናቂ አቋሙን እያሳየ ይገኛል፡፡ የአማካይ ስፍራ ተጫዋቹ ቴዲ በ2010 በሀምበሪቾ ዱራሜ ቆይታን በማድረግ በ2011 ደግሞ በአርባምንጭ ከተማ መልካም የውድድር ዓመትን በግሉ ካሳለፈ በኋላ ወደ ፋሲል ከነማ እና ወደ ቀድሞ ክለቡ ባህርዳር ከተማ ያመራል ተብሎ ቢጠበቅም የአሰልጣኝ ተመስገን ዳናውን አዲስ ክለብ ደቡብ ፖሊስን ዛሬ ተቀላቅሏል፡፡

11 ተጫዋቾች ያስፈረሙት ቢጫ ለባሾቹ ነገ የቅድመ ውድድር ዝግጅታቸውን በሀዋሳ ይጀምራሉ፡፡


© ሶከር ኢትዮጵያ