የዮናስ በርታ ማረፊያ አዳማ ሆኗል

በደቡብ ፖሊስ የአንድ ዓመት ቆይታ የነበረው የተከላካይ አማካዩ ዮናስ በርታ ዛሬ የአዳማ ከተማ አዲስ ፈራሚ ሆኗል፡፡

በዝውውር ሂደቱ ጅማሮ በርከት ያሉ ተጫዋቾች በአዲስ መልክ እና ነባሮችን ደግሞ ውላቸውን አራዝሞ የነበረው አዳማ ከተማ ከደመወዝ ክፍያ ጋር በተያያዘ የተወሰኑትን ለማጣት ተገዷል፡፡ ዛሬ ደግሞ ተቀዛቅዞ ከቆየበት የዝውውር ተሳትፎው በመመለስ የአማካይ ስፍራ ተጫዋቹ ዮናስ በርታን አስፈርሟል፡፡

የቀድሞው የባህር ዳር ከተማ የተከላካይ አማካይ ባለፈው ዓመት በደቡብ ፖሊስ በግሉ የተሳካ ዓመትን ያሳለፈ ሲሆን በኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ስብስብ ውስጥም መካከተት ችሏል። ተጫዋቹ ከቀድሞ ክለቡ ባህር ዳር ጋር ስሙ ቢያያዝም ዛሬ ለአዳማ ከተማ ፊርማውን አኑሯል፡፡


© ሶከር ኢትዮጵያ