ደደቢቶች አምስተኛ ተጫዋቻቸውን አስፈረሙ

በትናንትናው ዕለት የአራት ተጫዋቾች ዝውውር ያጠናቀቁት ሰማያዊዎቹ ከድር ሳልህን አስፈረሙ።

በወልዋሎ የሁለት ዓመት ቆይታው ቡድኑ ወደ ፕሪምየር ሊጉ እንዲያድግ ከፍተኛ አስተዋፅኦ የነበረው እና በኢትዮጵያ ቡና እና አውስኮድ መጫወት የቻለው የመስመር አጥቂው የአምናውን የውድድር ዓመት በአዲስ አበባ ከተማ በመጫወት አገባዶ ሰማያዊዎቹን በአንድ ዓመት ውል ተቀላቅሏል።

ሰማያዊዎቹ ቀደም ብለው ጌታቸው ዳዊትን አዲስ አሰልጣኝ አድርገው በመቅጠር በትናንትናው ዕለት ሃፍቶም ቢሰጠኝ፣ ክፍሎም ሐጎስ፣ ዳንኤል አድሐኖምና ክብሮም ግርማይን ማስፈረማቸው ይታወሳል።

በዝውውር መስኮቱ ዘግይተው በመግባት እስካሁን ድረስ አምስት ተጫዋቾች ያስፈረሙት ደደቢቶች በቀጣይ ቀናት ተጨማሪ ዝውውሮች ያደርጋሉ ተብሎ ይጠበቃል።


© ሶከር ኢትዮጵያ