ሴካፋ ከ20 ዓመት በታች | ዩጋንዳ እና ብሩንዲ ሲያሸንፉ ኤርትራ ነጥብ ጥላለች

በሴካፋ ከ20 ዓመት በታች ዋንጫ የዛሬ ውሎ ብሩንዲ ሶማልያን ስታሸንፍ ስድስት ጎሎች በታዩበት ጨዋታ ኤርትራ እና ሱዳን ነጥብ ተጋርተዋል። ዩጋንዳም ጅቡቲን ድል አድርጋለች።

ቀድሞ የተካሄደው የብሩንዲ እና ሶማልያ ጨዋታ ሲሆን ውጤቱም ብሩንዲ ሁለት ለአንድ አሸንፋለች። ማራኪ ጨዋታ እና ሳይጠበቅ ተመጣጣኝ ፉክክር ታይቶበታል የተባለው ጨዋታ ብሩንዲ በሐሚሙ ሐኪዝማና እና ልዊስ ሮምዬ ጎሎች ተጋጣሚዋን ስታሸንፍ የሶማልያ ብቸኛ ግብ አሕመድ አብዱላሂ ዓብዲ አስቆጥረዋል።

ሁለተኛ የእለቱ ጨዋታ የነበረው እና ስድስት ግቦች የታዩበት የኤርትራ እና ሱዳን ጨዋታ ሲሆን ውጤቱም ሶስት ለ ሶስት ተጠናቋል።

የዕለቱ ሶስተኛ ጨዋታ አዘጋጇ ዩጋንዳ ጅቡቲን የገጠመችበት ሲሆን ዩጋንዳ 5-1 አምስት ለአንድአሸንፋለች። ጎሎቹን ጀስቲን ኦፒሮ፣ ስቴፈን ሰራውዳ (ሁለት)፣ ኢቫን ቦጌሬ እና ዒስማ ሙግሊሲ ሲያስቆጥሩ የጅቡቲ ብቸኛ ግብ ካሊድ ዑስማን አስቆጥሯል።


© ሶከር ኢትዮጵያ