ደቡብ ፖሊስ ተጨማሪ ተጫዋቾችን አስፈረመ

ደቡብ ፖሊስ ተከላካዩ ተክሉ ታፈሰ እና አማካዩ ምትኩ ማመጫን አስፈርሟል፡፡

የቀድሞው የሀላባ ከተማ የመሀል ተከላካይ ባለፉት ዓመታት በወላይታ ድቻ ቡድኑን በቋሚነት ከማገልገሉ በተጨማሪ አምበል ሆኖ በርካታ ጨዋታዎችን የመራ ሲሆን አሁን ደግሞ በአንድ የውድድር ዓመት ውል ደቡብ ፖሊስን ተቀላቅሏል።

የአማካይ ስፍራ ተጫዋቹ ምትኩ ማመጫ ሌላው የሀዋሳውን ክለብ የተቀላቀለ ወጣት የአጥቂ አማካይ ስፍራ ተጫዋች ሆኗል፡፡ ከሀዋሳ ከተማ የታዳጊ ቡድን ተገኝቶ በዋናው ቡድን መጫወት የቻለው ይህ ተጫዋች በዲላ ከተማ እና በ2011 በሀላባ ከተማ ቆይታን ካደረገ በኋላ በታዳጊ ዕድሜው ካሰለጠው ተመስገን ዳና ጋር በድጋሚ ያገናኘውን ዝውውር ፈፅሟል፡፡


© ሶከር ኢትዮጵያ