የዱባዩ ጉዞ የመሳካት ጉዳይ ጥያቄ ምልክት ውስጥ ገብቷል

ሦስት ክለቦች ይሳተፉበታል የተባለው የዱባይ የቅድመ ውድድር ዝግጅት የመደረጉ ነገር ጥያቄ ምልክት ውስጥ ገብቷል።

ከአንድ ወር ገደማ በፊት ሶስት የትግራይ ክለቦች ወልዋሎ፣ ስሑል ሽረ እና መቐለ 70 እንደርታ በኢትዮ ነጃሺ የጉዞ ወኪል አማካኝነት የቅድመ ውድድር ዝግጅት እና የአቋም መለኪያ ጨዋታዎች ለማድረግ ወደ ተባበሩት ዓረብ ኤሜሬቶች እንደሚያቀኑ በኖብል ሃውስ ሆቴል በጠሩት የጋዜጣዊ መግለጫ ቢገልፁም ጉዞው ከታሰበበት ወቅት ለሁለት ጊዜያት መራዘሙ ይታወቃል። አሁን ደግሞ ወደ ስፍራው የሚያቀኑበት ዕድል የጠበበ እንደሆነ ለጉዳዩ ቅርብ ከሆኑ ግለሰብ ሰምተናል።ምንም እንኳ ጉዞው የተሰናከለበት ምክንያት ግልፅ ባይሆንም ከገንዘብ ጋር የተያያዘ ጉዳይ ሳይሆን እንዳልቀረም ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።

ይህ ለሁለት ጊዝያት የተራዘመው ጉዞ የሚቀር ከሆነም የመካሄዱ ነገር አጠራጣሪ የነበረው የትግራይ ክልል ዋንጫ ሊካሄድ እንደሚችል ይገመታል።


© ሶከር ኢትዮጵያ