ሴቶች ዝውውር | ጌዲኦ ዲላ ዘጠኝ ተጫዋቾችን ሲያስፈርም የሁለት ነባሮችን ውል አራዝሟል

የሴቶች ፕሪምየር ሊግ አንደኛ ዲቪዚዮን ተሳታፊው ጌዲኦ ዲላ በለቀቁት ወሳኝ ተጫዋቾች ምትክ የዘጠኝ አዳዲስ ተጫዋቾች ዝውውር ሲያጠናቅቅ የሁለት ነባሮችንም ውል አራዝሟል፡፡

አሰልጣኝ እንዳልካቸው ጫላ ለሶከር ኢትዮጵያ እንደገለፁት በለቀቁ ወሳኝ ተጫዋቾች ምትክ በ2011 በየክለቦቻቸው ንቁ ተሳትፎ የነበራቸውን ዘጠኝ አዳዲስ ተጫዋቾችን ወደ ክለባቸው የቀላቀሉ ሲሆን አዲስ ፈራሚዎቹም መኪያ ከድር (ግብ ጠባቂ ከንፋስ ስልክ ላፍቶ)፣ ቤተልሄም ዮሀንስ (ግብ ጠባቂ ከዲላ አካባቢ)፣ ቃልኪዳን ተስፋዬ (ተከላካይ ከጥረት ኮርፖሬት)፣ ቤተልሄም አስረሳኸኝ (ተከላካይ ከአዳማ ከተማ)፣ ነፃነት ሰውአገኝ (አማካይ ከጥረት ኮርፖሬት)፣ ደራ ጎሳ (አማካይ ከጥሩነሽ ዲባባ)፣ ቤዛ ታደሰ (ፎቶ ከላይ / አጥቂ ከአአ ከተማ)፣ ትዝታ ፈጠነ (አጥቂ ከድሬዳዋ ከተማ)፣ ነቢያት ሀጎስ (አጥቂ ከድሬዳዋ ከተማ) መሆናቸውን ገልፀዋል።

በ2011 በክለቡ መልካም የውድድር ዓመት ያሳለፉት የአማካይ ስፍራ ተጫዋቿ እና የቡድኑ አምበል ትርሲት መገርሳ እንዲሁም አጥቂዋ ድንቅነሽ በቀለ ለተጨማሪ ዓመት በዲላ ለመቆየት ውላቸውን ማደስ ችለዋል፡፡


© ሶከር ኢትዮጵያ