ደደቢቶች የሁለገብ ተጫዋቻቸውን ውል አራዘሙ

ባለፈው ዓመት በሊጉ ክስተት ከነበሩ ተጫዋቾች አንዱ የሆነው ሁለገቡ መድሃኔ ብርሃኔ ከሰማያዊዎቹ ጋር ለመቆየት ተስማምቷል።

ከደደቢት ሁለተኛ ቡድን አድጎ ላለፉት ዓመታት ከዋናው ቡድን ጋር ቆይታ የነበረው ተጫዋቹ በ2010 የውድድር ዓመት ለዋናው ቡድን በቋሚነት መጫወት ጀምሮ ባለፈው ዓመት በመስመር ተከላካይነት፣ በመስመር ተጫዋችነት እና በአጥቂ ቦታ ላይ መጫወቱ ይታወሳል።

ባለፈው ዓመት በግሉ ጥሩ ዓመት ያሳለፈው እና ባለፉት ሳምንታት ከሌሎች የፕሪምየር ሊጉ ክለቦች ስሙ ሲያያዝ የቆየው ተጫዋቹ ቀጣይ ውድድር ዓመት በተፈጥሯዊ የመስመር ተከላካይነቱ የሚሰለፍ ከሆነ ለቋሚነት ከዳንኤል አድሐኖም ጋር የሚፎካከር ይሆናል።


© ሶከር ኢትዮጵያ